የዘላለም ሕይወትSample

በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሁሉም ብሔሮችና እና ቋንቋዎች አሉ።
በእግዚርብሔር ቃል ውስጥ የእስራኤል ሕዝብ ልዩ ቦታ አላቸው። እግዚአብሔር ከአባታቸው ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን በመገባቱ፤ ይህን ሕዝብ ልዩ ተወካዮቹ እንዲሆኑ መርጧል። ምንም እንኳን ጥሪያቸውን ባይፈጽሙም ብዙ አይሁዶች የአብርሃም ዘሮች በመሆናቸው ይኮሩ ነበር። እንዲያውም አይሁዶች ብቻ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑ ያስቡ ነበር።
ይህ ትክክል እንዳልሆነ የእግዚርብሔር ቃል በግልጽ ይናገራል። ለምሳሌ መዝሙረ ዳዊት 22፡27-28 እና ዘካርያስ 2፡11 ተመልከት። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው አይሁዶች ያልሆኑትንም ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ እና በአንድነት ወደ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሊያስገባቸው ነው። ደቀ መዛሙርቱን ወንጌሉን እስከ ምድር ዳርቻ እንዲያደርሱ እና አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዝሙር እንዲያደርጉ ጌታ ኢየሱስ አዟቸው ነበር። በዚህም ተልዕኮ ምክንያት፤ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በርካታ ክርስቲያኖች ይገኛሉ።
በራዕይ 7 ላይ፣ መንግሥተ ሰማያትን በጨረፍታ እንመለከታለን። ከሁሉም ብሔር፣ ከሁሉም ነገዶችና ሕዝቦች የተውጣጡ ብዙ ሕዝብ፤ በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት ለዘላለም በደስታ ውስጥ ናቸው። ስለሆነም እግዚአብሔር አምላካችን አንዳንድ ብሔሮች ወይም ሕዝቦች ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉም ሰዎች እንዲድኑ ይፈልጋል።
በዓለም ዙሪያ በሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ባሉት ልዩ ልዩ ህዝቦች ትደቃለህ?
About this Plan

ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።
More
Related Plans

Ruth: A Story of Choices

Slaying Giants Before They Grow

EquipHer Vol. 24: "Who’s Economy Are You Working For?"

Discover God’s Will for Your Life

EquipHer Vol. 26: "How to Break the Cycle of Self-Sabotage"

Drawing Closer: An Everyday Guide for Lent

Made New: Rewriting the Story of Rejection Through God's Truth

Finding Strength in Stillness

Conversation Starters - Film + Faith - Forgiveness, Mentors, Tornadoes & More
