YouVersion Logo
Search Icon

የዘላለም ሕይወትSample

የዘላለም ሕይወት

DAY 5 OF 9

ሰውነታችንም ይታደሳል።

ትላንት የሥጋ ሞት የዘላለምን ሕይወትን እንደማያቋርጥ አይተናል። ይህ ማለት ሰውነታችን አስፈላጊ አይደለም ወይም ከእግዚአብሔር የወደፊት ፈቃዱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ማለት አይደለም።

ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጆችን ለመፍረድና አዲስ ምድርን ለመፍጠር ሲመለስ የእኛም አካል ይነሣል። ከትንሣኤ በኋላ የክርስቶስን ክቡር ሥጋ ለመምሰል ይለወጣል፤ የማይሞት እና የማይበሰብስ ሆኖ ይነሳል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ከዘር ከመዝራት ጋር አመሳስሎታል። ሟች አካላችን በድካምና በውርደት የተዘራ ነው፤ ሁላችንም በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንደምናውቀው፣ የሞተና የሚበሰብስ አካል ክብር ባይኖረውም፤ ሰውነታችን በክብር ይነሳና ከመንፈሳችን ጋር እንደገና በአምላካችን አዲሱ ምድር ላይ ለዘላለም ይኖራል።

ይህን ዘላለማዊነት ከአመላካችን ከእግዚአብሔር ጋር የምንሆነው በመንፈሳዊነት ብቻ ሳይሆን፤ በተለወጠ አካል እና በንጹህ መንፈስ በመሆናችን ነው። እግዚአብሔር አምላክ ለሰውነታችን ዋጋ በመስጠቱ እንዲታደስ እንጂ እንዲጠፋ አይፈልግም።

እርሶስ ለሰውነትዎ ዋጋ ይሰጣሉ?

About this Plan

የዘላለም ሕይወት

ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።

More