YouVersion Logo
Search Icon

የዘላለም ሕይወትSample

የዘላለም ሕይወት

DAY 7 OF 9

በአዲሱ ምድር ላይ ሞት እና ስቃይ የለም።

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም እና ሔዋን አስቀድሞ እንዳስጠነቀቃቸው፤ በእርሱ ላይ ባመፁ ጊዜ ኃጢአታቸው ሥቃይና ሞትን አስከትሏል። ‘’የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና" ( ሮሜ 6:23)።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መከራ እና ስቃይ የሰው የሕይወት ክፍል ሆኗል። አንዳንዶቹ ስቃዮች በሰዎች የሚከሰቱ፣ ሌሎች ዓይነት መከራዎች ደግሞ በዚህ ዓለም ውድቀት ወይም በራሳችን የተሳሳተ የሕይወት ምርጫ የመጡ ናቸው። በዚህም ምክንያት ከጽጌረዳ አበባ እሾህ በላይ ሕይወት በመከራ የተሞላ ሆነ። ሙሴ እንኳን አማረረ፡- "የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው" (መዝሙረ ዳዊት 90:10)።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአትን ዋጋ ለሰው ዘር ሁሉ ሲከፍል፤ የኃጢአት ውጤት የሆነውን ሞትን አሸንፏል። በኢሳይያስ 25፡8 ላይ ጌታ ''ሞትን ለዘላለም እንደሚውጥ'' እና ''ከፊት ሁሉ እንባን እንደሚያብስ'' የተስፋው ቃል ተፈጸመ። እነዚህ የኃጢአትና የውድቀት ውጤቶች የሆኑት፤ 'ኀዘን፣ ለቅሶ እና ሥቃይ' በዘላለም ክብሩ ውስጥ አይኖሩም።

ከአምላካችን ከእግዚአብሔር እና ካመኑት ወገኖቻችን ጋር በገነት ያለመከራ ለዘላለም መኖር እጅግ የሚያስደስት ህይውት ነው።

About this Plan

የዘላለም ሕይወት

ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።

More