YouVersion Logo
Search Icon

የዘላለም ሕይወትSample

የዘላለም ሕይወት

DAY 2 OF 9

የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የዘላለም ሕይወትን እንደ አንድ ‘ልዩ ሕይወት’ ይገልጸዋል። ይህም ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ላይ የተመሠረተ ነው። የዘላለም ሕይወት ‘እግዚአብሔርን ማወቅ’ ማለት ነው። ይህም የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ብቻ ነው። “ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ ዕቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው አምላክ እርሱ ገለጠው” (ዮሐንስ 1፡18)።

ብዙ ሰዎች ስለ አምላክ ያላቸው ግንዛቤ ውስን ቢሆንም፣ “አምላክ የሆነ አንድ ሀይል” ሊኖር እንደሚችል ይገምታሉ። አንዳንዶች በህይወት ልምዳቸው፣ በሳይንሳዊ ወይም ፍልስፍናዊ ግንዛቤዎች፣ ወይም በሃይማኖታዊ መጽሃፎች ላይ በመመስረት ስለ አምላክ ብዙ እንደሚያውቁ ያስባሉ። ነገር ግን ‘እግዚአብሔርን ማወቅ’ የአዕምሮ እውቀት ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ጋር ያለን የግል ግንኙነት ነው።

ችግሩ እኛ ሰዎች በተፈጥሮአችን ኃጢአተኞች ስለሆንን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ክፉኛ ተጎድቷል! ከፈጣሪያችን ጋር ትክክለኛ የሆነ ግንኙነት ስለሌለን በተፈጥሮአችን የዘላለም ሕይወት የለንም። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል፣ “በበደላችን ሙታን ነን” (ኤፌሶን 2፡5)።

ጌታ ኢየሱስ ዳግም ሕያዋን ሊያደርገን መጥቷል። የኃጢአት ይቅርታ በማግኝት ከጌታ ጋር አዲስ የሕይወት ግንኙነት እንዲኖረን አድርጓል። ከእርሱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካለን፣ ሕይወታችን ሙሉ በሙሉ ይለወጣል። ይህንንም አዲስ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈሳዊ ቋንቋ 'ዳግም መወለድ' ብሎ ይጠራዋል። ይህ ዘላለማዊ ሕይወት የሚጀምረው ዳግመኛ ከተወለድንበት ቀን ጀምሮ ሲሆን፣ ከሥጋዊ ሞት በኋላ ለዘላለም የሚቀጥል ይሆናል።

ጌታ ኢየሱስን ታውቀዋለህን?

About this Plan

የዘላለም ሕይወት

ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።

More