እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ቀን {{ቀን}} ከ15

የተስፋ ምንጭ ምንድን ነው?

''በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር እናንተን ከመጀመሪያ አንሥቶ በመንፈስ ተቀድሳችሁና በእውነትም አምናችሁ እንድትድኑ መርጧችኋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ተካፋዮች እንድትሆኑም በወንጌላችን አማካይነት ጠርቷችኋል። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በአንደበታችንም ሆነ በመልእክታችን ያስተላለፍንላችሁን ትምህርትአጥብቃችሁ ያዙ። ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ደግሞም እኛን የወደደንና በጸጋው የዘላለም መጽናናትና መልካም ተስፋን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣ ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎ ሥራና በቃል ሁሉ ያበርቷችሁ'' (1ተሰሎንቄ 2፡13-17)።

ተስፋችን ጠንካራ እንዲሆን ከተፈለገ ጠንካራ መሰረት ያስፈልገዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው ተስፋችን በእግዚአብሔር የተሰጠን በጸጋ ነው። እርሱ የጸጋ አምላክ ባይሆን ኖሮ የተስፋ ሰዎች አንሆንም ነበር። ስለ ወደፊቱ ማሰብ እና አዎንታዊ ሀሳቦች እንዲኖረን እንችል ነበር፣ በተጨማሪም በተስፋም ላይ ጠንካራ መተማመን አይኖረንም ነበር።

እዚህ ላይ ጳውሎስ ስለ ሰው ልጆች እየተናገረ አይደለም ነገር ግን ስለ 'እኛ' ነው። ታዲያ እግዚአብሔር ይህንን በጸጋው መልካም ተስፋን የሰጠው ለማን ነው? ለኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ለተገዙ እና በእግዚአብሔር ፍቅር እና አባትነት ላረፉ ሰዎች ሁሉ ነው። እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን 'ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ' የሚሉ እና እግዚአብሔርን 'አባታችን' የሚሉ ናቸው።

ከላይ በተገለጸው የእግዚአብሔር ቃል ላይ እንደተገለጸው በድነት የእግዚአብሔርን ጸጋ አግኝተናል። የእግዚአብሔር ታላቅ የማዳን ሥራ በሕይወታችን ውስጥ 'የተስፋችን' መሠረት ነው።

ለኢየሱስ ጌትነት ትገዛለህ? በእግዚአብሔር አባትነት ላይ አርፈሀል?

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/