እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ቀን {{ቀን}} ከ15

ተስፋ የእምነት አካል ነው

''እምነት ተስፋ ያደረግነው ነገር እንደሚፈጸም ርግጠኛ የምንሆንበት፣ የማናየውም ነገር እውን መሆኑን የምንረዳበት ነው'' (ዕብራውያን 11፡1)።

“እንግዲህ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው” (1ኛ ቆሮንቶስ 13፡13)።

ከላይ ዕብራውያን ላይ እንደምናየው፤ በእምነት እና በተስፋ መካከል ያለውን ግንኙነት ያብራራል። እምነት የማናያቸውን ነገሮች ያስረዳናል። ስላለፈው፣ ስለአሁኑ እና ስለወደፊቱ በእግዚአብሔር ቃል እንድንታመን ያደርገናል። ተስፋ የምናደርጋቸውን ነገሮች እውነተኛ የሚያደርገው እምነት ነው።

ይህ በእምነት እና በተስፋ መካከል ያለው ግንኙነት አማኞች ከእግዚአብሔር የሚጠብቁትን ነገር ማለትም፥ እግዚአብሔር ስለወደፊቱ ቃል የገባልንን መልካም ነገሮች ግልጽ እና እንድንረዳው ያደርገዋል። ይህም ምድራዊ ሕይወታችንን እና መንፈሳዊ በረከቶቻችንን ያጠቃልላል።

በተጨማሪም ኃጢአት፣ ስቃይ እና ሞት የሌለበትን አዲስ ምድር፤ ከጌታ ጋር የዘላለም ሕይወትን ያካትታል። እነዚህ ነገሮች አሁን ልናያቸው አንችልም፤ ነገር ግን በእምነት ይህ ተስፋችን እውን እንደሚሆን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

ይህ የመዳን እምነት አለህ?

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/