እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ቀን {{ቀን}} ከ15

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ

''እግዚአብሔር ዐለቴን፣ 'ለምን ረሳኸኝ? ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?' እለዋለሁ'' (መዝሙር ዳዊት 42፡9)።

ይህን ክፍል ዳዊት የጻፈው በተጨነቀ እና በታወከ ጊዜ ነበር። እግዚአብሔር በጣም የራቀው፣ የረሳው እንዲሁም በፊቱ እንደቀደመው ዘመን ያልታሰበ ስለመሰለው የዳዊት ልቡ ተሰበረ። ዳዊትም በጌታ ያለውን ተስፋ ለመጠበቅ የሚያደርገውን ትግል እንመለከታለን።

እግዚአብሔርን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ተስፋ ማድረግ በተፈጥሮ የሚገኝ አይደለም። በችግሮቻችን እና በሀዘኖቻችን ውስጥ ስንሆን በቀላሉ ተስፋችን ሊሸነፍ እንዲሁም ሰዎች የእግዚአብሔርን ቸርነት ከእኛ ጋር መኖሩን ሲጠራጠሩ ልናይ እንችላለን። ዳዊት ላዘነውና ለተጨነቀው መንፈሱ የእግዚአብሔርን ታማኝነት ማሰብ እንዳለበት ያውቅ ነበር። የእሱ ተስፋ፥ ሁኔታው ​​ወደ ተሻለ እንዲለወጥ ብቻ አልነበረም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ ያድነኛል የሚል እምነት ነበረው። የመፅሐፍ ቅዱሳዊው ተስፋ ዋናው ነገር ይህ ነው። እግዚአብሔር ጣልቃ እንደሚገባ መተማመን። ይህ ተስፋ በእግዚአብሔር የማይለወጥ መልካምነት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ እውነተኛ ነው።

በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ፣ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ ስለማድረግ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እናነብባለን።

ቅዱሳት መጻሕፍት

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/