እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

ተስፋ ከፈተና ይጠብቅሃል
ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች እና ለተሰሎንቄ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በጨለማ ውስጥ መኖርን እና በብርሃን ውስጥ መኖርን ልዮነቱን ያስረዳል። በጨለማ ውስጥ መኖር ማለት ያለ እግዚአብሔር መኖር ማለት ነው። ይህ "ፍሬም ከሌለው የጨለማ ሥራ" እንደ ዝሙት፣ ስግብግብነት እና የስንፍና ንግግርን ያስከትላል፣ አማኞች "በጌታ ብርሃን" ናቸው፣ "የቀን" ናቸው።
ይህ በሕይወታቸው ውስጥ መታየት አለበት። ከጨለማ ሥራ ርቀው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መኖር አለባቸው። በተለይ በመንፈሳዊ ጨለማ በተከበብን ጊዜ ይህ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ብዙ ጊዜ፣ እምንትን ለማጉደል፣ ለመዋሸት፣ ለመመኘት ወይም ሌሎችን ለመበደል እንፈተናለን።
እነዚህን ፈተናዎች ማሸነፍ ትግል ነው። ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ጥሩር እና የራስ ቁር የጻፈው ለዚህ ነው። እራሳችንን ለመከላከል እና ኃጢአትን ለመዋጋት እነዚህ ያስፈልጉናል።
ጳውሎስ “የመዳን ተስፋ” እንደ ራስ ቁር ነው ብሏል። ይህ ተስፋ ፈተናዎችን ግምት ውስጥ ስለሚያስገባ ጊዜያዊ የኃጢአት ደስታን ለመካድ ስሜታዊ እና ውስጣዊ ጥንካሬ ይሰጠናል። ምድራዊ ነገሮች እግዚአብሔር ለልጆቹ ቃል ከገባላቸው ‘’ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብር’’ ጋር ሲነጻጸሩ ቀላል እና ምንም ናቸው (2ቆሮንቶስ 4:17)።
እራስዎን ከፈተናዎች እንዴት ይከላከላሉ?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/