እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ቀን {{ቀን}} ከ15

ሕያው የሆነ ተስፋ

አንድ የተለመደ አባባል እንዲህ ይላል: 'ሕይወት ካለ፣ ተስፋ አለ’’። ይህ አባባል በኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ ትርጉም አግኝቷል። ሐዋርያው ጴጥሮስ ለአማኞች በጻፈው መልዕክት፥

‘’በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣ እንዲሁም በሰማይ ለማይጠፋ፣ ለማይበላሽና ለማይለወጥ ርስት እንደ ገና ወለደን” (1ኛ ጴጥሮስ 1፡3)።

"ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለዚህች ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን። ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በርግጥ ከሙታን ተነሥቷል” (1 ቆሮንቶስ 15፡19-20)።

ኢየሱስ ለሰው ልጆች ኃጢአት ዋጋ ከፍሏል። በእኛ ቦታ በመሞት ድል አድርጓል። ትንሣኤው ሞት መውደቁን አረጋግጧል።

“ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ፣ እርሱ ራሱ ደግሞ ያንኑ ተካፈለ፤ ይኸውም በሞት ላይ ኀይል ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ ኀይል እንዲደመስስ ነው” (ዕብ. 2፡14) ።

ክርስቲያኖች የዘላለም ሕይወት ስላገኙ ከእንግዲህ ሞት አያስፈራቸውም። በሞት ጊዜም እንኳ ሕያው ተስፋ አላቸው። በእርግጥ ይህ ሥጋዊ ሞት ለሰው ልጆች የማይቀር ነገር ነው። ስለዚህ ለዚህ ምድራዊ ሕይወት ብቻ ተስፋዎች ካሉን፣ ይህ በመጨረሻ በጣም ዝቅ ያለ ተስፋ ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ይናገራል።

''በመጨረሻው ዘመን ሊገለጥ የተዘጋጀው ድነት እስኪመጣ ድረስ በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።” (1 ጴጥሮስ 1:4-5)

ይህ ሕያው ተስፋ አለህ?

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/