የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

About YouVersion

ጠቃሚነት

ባለፉት ትውልዶች፣ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የሚያገኙበት እድል በጣም የተወሰነ ነበር። በአሁኑ ጊዜ፣ ጉዳዩ ይሄ አይደለም። ይሁን እንጂ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የማግኘት እድል ያላቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች መልዕክቱ በሕይወታቸው ላይ እንደማይሰራ ያስባሉ። በተመሳሳይ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በዕለት ተዕለት ተሞክሮዎቻቸው መካከል ግንኙነት እንዳለ የሚያምኑ ሌሎች ሰዎች አሉ።

የመረጃ አብዮት

ባለፉት አስርት ዓመታት፣ በይነመረብ ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ ሰዎችን የሚያጎለብት አብዮት አምጥቷል። ማጋራት፣ ማበርከት፣ መፍጠር፣ ማሰራጨት እና ማስተላለፍ በመቻሉ፣ ለቀሪው ዓለም ማን እንደሆንን እና ምን እንደምናምን ለመግለጽ ቀላል ነው።

YouVersion

በ1996 ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ የLife.Church አላማ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የተሰጡ የክርስቶስ ተከታዮች እንዲሆኑ መምራት ነው። እንዲህ በማድረግ፣ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ከዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ጋር እንዲያገናኙ ለማገዝ አዳዲስ መንገዶችን ፈልገናል። የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እና ስልቶችን ስናስገባ ዘዴዎቻችን ለዓመታት ተለውጠዋል። ነገር ግን በዋነኝነት፣ ሰዎች በሕይወታቸው በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉም ሰው ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ለማሳየት እና ለማስተማር ያለማቋረጥ ስንጥር ትኩረታችን ቀጣይነት ያለው ጠቃሚነት ላይ ሆኖ ይቆያል። በLife.Church ጥረቶች YouVersion አዲስ ወሰን ገልጿል። አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዓለም ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ብቻ አንድን መሣሪያ እየገነባን ሳይሆን፣ በተጨማሪ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ለሕይወታቸው ያለውን ጠቀሜታ ሲያውቁ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነቶችን እንዲፈጥሩ እየሰራን ነው።