እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

በተስፋ ላይ ተስፋ አድርግ
“ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ ደግሞም እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎች በረከት ትሆናለህ'' (ዘፍጥረት 12፡2)።
አብርሃም ተስፋው በእምነት ላይ የተመሰረተ አማኝ ጥሩ ምሳሌ ነው። እግዚአብሔር ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገው ቃል ገብቶለታል። በዚያን ጊዜ አብርሃም 75 ዓመቱ ነበር። ነገር ግን ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ ምንም ነገር አልተፈጠረም። አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ልጅ ሳይወልዱ ቆዩ።
"ከዚህም በኋላ፣ የእግዚአብሔርቃል እንዲህ ሲል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፤ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ዋጋህምእኔው ነኝ።” አብራምም፣ “ጌታእግዚአብሔርሆይ፤ ያለ ልጅ የቀረሁ ስለ ሆንሁ፣ የቤቴ ወራሽየደማስቆ ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ ምን ትሰጠኛለህ?” አለው። “አንተ ልጆች ስላልሰጠኸኝ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም።” በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔርቃል እንዲህ ሲል መጣለት፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚከፈል ልጅ ወራሽህ ይሆናል።” ወደ ውጭም አውጥቶ፣ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስኪ መቍጠር ከቻልህ፣ ከዋክብቱን ቍጠራቸው፤ ዘርህም እንዲሁ ይበዛል” አለው። አብራም እግዚአብሔርን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቈጠረለት" (ዘፍጥረት 15፡1-2)። አብርሃም እምነቱ 'ከተስፋ' ጋር ነበር።
ለብዙ አሥርተ ዓመታት በትዳር ውስጥ የኖረች ልጅ የሌላት ሴት፣ የመውለድ ዕድሜዋ ካለፈ በኋላ በድንገት ማርገዟ በፍጹም የማይጠበቅ ነገር ነበር። አብርሃም ግን የእግዚአብሄርን ተስፋ ስላመነ ተስፋ አልቆረጠም። መቶ ዓመት ሲሆነው ልጁ ይስሐቅ ተወለደ። እግዚአብሔር ቃሉን ጠበቀ።
ለማመን የሚከብድህ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን አለ?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/