እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

ተስፋህን ለሌሎች ማስረዳት
ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ ማድረግ የግል ውሳኔ ነው፣ አንዳንዴም የግል ትግል ነው። የመዳን እምነትህን እና ከጌታ ጋር ያለህን ግንኙነት መጠበቅ በራስህ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ነገር ነው። ነገር ግን እምነትህን ከውጪው ዓለም መደበቅ አይቻልም። ይህ በአኗኗር ዘይቤህ፣ በምርጫህ፣ ለፈተና በምትሰጠው ምላሽ፣ ለሌሎች ሰዎች ያለህ አመለካከት - በመሠረቱ ሁሉም ነገር ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል። ይህም ሌሎች 'በእናንተ ስላዩት ተስፋ ምክንያት' እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው ይችላል። እንዲያስረዱ ሊጠየቁ ይችላሉ፤ ምክንያቱም፦ አስቅንትዋቸዋል ወይም የማወቅ ጉጉት አድሮባቸዋል ወይም አበሳጭቷቸዋል።
ለጥያቄዎቻቸው በትህትና ምላሽ መስጠት አስፈላጊ ነው። ''ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት'' (1ጴጥሮስ 3፡15)። ምላሽህ ስም አጥፊዎችን አሳፍሮ ወደ ኢየሱስ ሊመራቸው ይችላል። ባልደረቦችህ ወይም ጓደኞችህ የሚያውቁት ክርስቲያን አንተ ብቻ ልትሆን ትችላለህ፤ ምስክርህ ወንጌልን ለመስማት ብቸኛ ዕድላቸው ሊሆን ይችላል። ሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል በልባቸው አይቀበሉም። ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው የሚጠሩ ሰዎች እንኳን ቢሆኑ እንደሚቸገሩ መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠነቅቀናል። ''እውነትን ከመስማት ጆሯቸውን ይመልሳሉ፤ ወደ ተረትም ዘወር ይላሉ'' (2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡4)። ይህ ግን በውስጣችን ያለውን የተስፋ ምክንያት ለእነሱ እንዳናካፍል ጥሪያችንን አይለውጠውም።
ወንጌልን ከማን ጋር ማካፈል ትችላለህ?
ይህን የንባብ እቅድ ስላጠናቀቁ እናመሰግናለን። እንደተጠቀሙ ተስፋ እናደርጋለን። ስለ እግዚአብሔር እና ከእሱ ጋር እንዴት እንደሚኖሩ የበለጠ ለማንበብ ከፈለጉ፣ እባክዎን ድህረ ገፃችንን www.biblword.net
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/