እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ቀን {{ቀን}} ከ15

ተስፋ ሀዘንን ይለውጣል

በተሰሎንቄ የነበረችው የቀደመችው ቤተክርስቲያን የአንዳንድ አማኞች ሞት ገጥሟት ነበር። ይህ ደግሞ ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል ጥያቄ አስነስቷል። ከአዲሲቱ ምድር ይጎሉ ይሆን? -አይጎድሉም በማለት ጳውሎስ አንባቢዎቹን አጽናንቷል።

"ጌታ እስኪመጣ ድረስ የቀረን እኛ ሕያዋን የሆንን ያንቀላፉትን አንቀድምም" (1ኛ ተሰሎንቄ 15)።

የሥጋ ሞት መጨረሻ አይደለም። ለዘላለም ሕይወት እንቅፋት አይሆንም። በተቃራኒው፣ ይህን ኃጢአተኛ ምድራዊ ሕይወት ትተን ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ያደርገናል።

ጳውሎስ በሌላ ደብዳቤ ላይ፡- ''ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋራ መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ'' (2ኛ ተሰሎንቄ 5- 8)። የምንወዳቸው ሰዎች ቢሞቱ ማዘን ፍፁም ተፈጥሯዊ ነው። በአዲሲቷ ምድር ብቻ ሀዘን ይወገዳል። ነገር ግን የሞተው ሰው የጌታ ልጅ መሆኑን ካወቅን ልንጽናና ይገባናል።

“ወንድሞች ሆይ፤ አንቀላፍተው ስላሉ ሰዎች ሳታውቁ እንድትቀሩ አንፈልግም፤ ደግሞም ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሰዎች እንድታዝኑ አንሻም” (1ኛ ተሰሎንቄ 4፡13)።

ምንም እንኳን በሞት የተለዩን ዘመዶቻችንን ወይም ጓደኞቻችንን ክፉኛ ብንናፍቅም፥ 'ለነፍሳቸው መልካም ነው' የሚለውን መረዳት በጣም ማጽናኛ ነው፣ አንድ ቀን፣ ለዘላለም ከጌታ ጋር ለመሆን ከእነሱ ጋር እንገናኛለን።።

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/