እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

ተስፋህን በተሳሳቱ ነገሮች ላይ አታድርግ
‘’ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ከንቱ ትሆናለች፤ በኀይሉ የተመካበትም ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል" (ምሳሌ 11: 7)።
አብዛኛው ሰው ምቹ እና ትግል አልባ ህይወት ይመኛል። ጥቂት ምሳሌዎችን ለመጥቀስ፤ ጥሩ ጤንነት እንደሚኖራቸው፣ ሀብታም እና ተደማጭነት እንደሚሆኑ ወይም ጥሩ ሥራ እንደሚያገኙ ተስፋ ያደርጋሉ። በእነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች፣ የሚናፍቁትን እንደሚቀበሉ እርግጠኛ መሆን ደግሞ አይችሉም። በዚህ ውስጥ የእነሱ ብሩህ አመለካከት ሊጎዳ ይችላል። ከዚህም በላይ፥ በተስፋ እየጠበቋቸው ያሉት ነገሮች ጊዜያዊ፣ በሕይወት እስካሉ ብቻ የሚያስፈልጉ ናቸው። ሰዎች ይታመማሉ፣ የንግድ ገበያዎች ይከስራሉ፣ አውሎ ነፋሶች ወይም የመሬት መንቀጥቀጥ በጥንቃቄ የተያዙ ቤቶችን ያወድማሉ። ይህ ለሁላችንም አስፈላጊ የሆነ ማሳሰቢያ ነው።
ተስፋችን በምድራዊ ነገሮች ላይ ብቻ የሚያተኩር ከሆነ የሞኝነት ጉዞ ላይ ነን። ይልቁንም የእግዚአብሔርን መንግሥት መፈለግ አለብን። ይህ መንግሥት ፈጽሞ አይጠፋም። ያረፈ እና የተባረከ ሕይወት ለማግኘት ያለንን ተስፋም አያደበዝዘውም - ከዚህ ምድር ጀምሮ፣ ለዘላለም ወደ ሙላቱ ይደርሳል።
ተስፋህን በምን ላይ ነው እያደረግከው?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/