እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ቀን {{ቀን}} ከ15

ተስፋ ለመጠበቅ የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት

ክርስቲያናዊ ትዕግሥት የሚመራውና የሚጸናው በተስፋ ነው።

"በጽናትና ቅዱሳት መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ እንዲኖረን፣ ቀደም ብሎ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፏልና'' (ሮሜ 15፡4)። ጳውሎስ እንደገለጸው የክርስቲያን ተስፋ የሚጸናው በቅዱሳት መጻሕፍት ማበረታቻ ነው። ስለዚህ መጽናት የሚገኘው የእግዚአብሔርን ቃል በማሰላሰል ነው። በመከራ ወቅት የእግዚአብሔርን እርዳታ ስላገኙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማንበብ አበረታች ሊሆን ይችላል። ስለ እግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች ታማኝነት ማንበብ ጥሩ ነው - በተወሰኑ ግለሰቦች ህይወት ውስጥ በተጨማሪም በዘመናት ውስጥ ስላለው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ አጠቃላይ ገጽታ ያሳየናል።

የማይሻረው የጌታ ቸርነት ላይ እንድናተኩር የሚያደርጉን በርካታ መዝሙራት እና ትንቢቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ። ሁሉንም ቅዱሳት መጻሕፍት ተግተን ማጥናታችን ከሐሰት ትምህርትና ማታለል ጸንተን እንድንቆም ይረዳናል። ጳውሎስ በመልዕክቱ የመጽሐፍ ቅዱስ አላማ ይህ መሆኑን አስገንዝቦናል።

መደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስርአት ቢኖረን መልካም ነው። በዚህ መንገድ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ለሚመጣው አስቸጋሪ ሁኔታ ጠንካራ መሠረት ይኖረናል።

“እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል።ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ በዐለትም ላይ ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የማያውለው ግን ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራን ሞኝ ሰው ይመስላል።ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም የከፋ ነበር” (ማቴዎስ 7፡24-27)።

ኢየሱስ ይህንን ዝናብ፣ ጎርፍና ነፋሳትን መቋቋም ይችል ዘንድ ቤቱን በዓለት ላይ ከሚሠራው ጠቢብ ሰው ጋር አነጻጽሮታል:- ይህም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ተስፋህን በእግዚአብሔር ቃል ትመግባለህ?

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/