እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ቀን {{ቀን}} ከ15

መንፈስ ቅዱስ በተስፋ ይሞላናል

ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የተስፋን ማረጋገጫ መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ተመለከትን፤ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረን ማጥናት እንዳለብን ተገንዝበናል። ሆኖም ግን ይህን ተስፋ በራሳችን ጥረት መጠበቅ አንችልም።

"በርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስስላችሁ ነው"(ሮሜ 15፡13)።

መንፈስ ቅዱስ ነፍሳችንን የሚመግብበት መንገዶች አሉት። ተስፋችን የተደገፈው፥ 'በተስፋ አምላክ' እና 'በመንፈስ ቅዱስ ኃይል' ላይ ነው። እርሱ ሊያድነን፣ የሚያስፈልገንን ጥንካሬ ሊሰጠን እና በደስታ እና ሰላም ሊሞላን ይችላል። እርሱ 'በተስፋ እንድንበዛ' ያደርገናል።

ደስታና ሰላም የመንፈስ ፍሬዎች ናቸው። ኢየሱስ ይህን ፍሬ ማፍራት የምንችለው እንዴት እንደሆነ በግልጽ ተናግሯል፡- “እኔ የወይን ተክል ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ማንም በእኔ ቢኖር እኔም በርሱ ብኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና'' ( 15፡5)። እግዚአብሔር አብ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ እዚህ ጋር ሁሉም ሲሳተፋ እናያቸዋለን፤ አንድ ላይ አንድ እውነተኛ አምላክ ናቸው። ከእርሱ ጋር የቅርብ ግንኙነት ካለን በተስፋ ይሞላናል።

በእግዚአብሔር ትኖራለህ?

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/