እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ቀን {{ቀን}} ከ15

ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ አስተምሯቸው

''እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን'' (መዝሙር 78፡4)።

ይህ ክፍል የእግዚአብሔርን ባሕርይ እና የከበረ ሥራ የማወቅን አስፈላጊነት በተመለከተ ነው፣ የእስራኤል ታሪክ ሰዎች እግዚአብሔርን ሲረሱ፣ ከእርሱ ሲርቁ እና ውጤቱን ሲጋፈጡ የሚያሳይ በምሳሌዎች የተሞላ ነው። ስለዚህ አሳፍ ይህን መዝሙር ጻፈው ለአባቶች የሰጠውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አድማጮቹን "እግዚአብሔርን ድንቅ ሥራውን" እንዲያስተምሩ ያሳስባቸዋል።

ትውልድ ሁሉ ጌታን ማወቅ አለበት። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ራሱን ስለማያሳይ፤ የቀደሙት ትውልዶች:- በራሳቸው የተለማመዱትን፣ ከወላጆቻቸው እና ከቀደሙት የሰሙትን እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያነበቡትን የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራዎች ማስተላለፍ የቀደሙት ትውልዶች ሃላፊነት ነው። ይህም ልጆችን ጌታ መልካም፣ ሁሉን ቻይ እና የታመነ እንደሆነ ያስተምራቸዋል። ''እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእርሱንም ሥራ አይረሱም፤ ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ''(መዝሙር 78፡7)።

ወላጆች የራሳቸውን እምነት እና ተስፋ ወደልጆቻቸው እንደሚያልፍ ማረጋገጥ አይችሉም፤ ነገር ግን እነሱን ማስተማር እና የእግዚአብሔርን ቃል መረዳታቸውን ማረጋገጥ የወላጅ ኃላፊነት ነው። ይህ እውቀት ወላጆች ለልጆቻቸው ሊሰጡ የሚችሉት እጅግ ውድ ስጦታ ነው።

ወላጆችህ ስለ አምላክ አስተምረውሃል?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/