እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

መከራዎች የክርስትናን ተስፋ አያጠፉም
የሰው ተስፋ በብስጭት እና በመሰናክሎች ይጠፋል። ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ላይ ያለው ተስፋ አይጠፋም። ነቢዩ ኤርምያስ አንድ ሙሉ የሰቆቃ መጽሐፍ ጽፏል። የኢየሩሳሌምን ከተማ መውደቅና የነዋሪዎቿን ሰቆቃ ተመልክቷል፣ ይህም በጥልቅ ነክቶታል። ''ነፍሴ ሰላምን ዐጣች፤ ደስታ ምን እንደ ሆነ ረሳሁ'' (ሰቆ. 3፡17)። በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥም ቢሆን ኤርምያስ የጌታን ጽኑ ፍቅር አስታወሰ፣ ተስፋም ሰጠው። ''ሆኖም ይህን ዐስባለሁ፤ እንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔርታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና'' (ሰቆ. 3፡21:22)።
ሐዋርያው ጳውሎስም ልምምዱን አካፍሎናል። ይህም ለገጠመው መከራ ተፈጥሯዊ ምላሽ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ቃል እርሱም፦ ''በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን። ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም'' (ሮሜ 5፡3-5)።
መከራ አጋጥሞህ ያውቃል? ይህ በአንተ ተስፋ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳደረ?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/