እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።ናሙና

የፍጥረት ተስፋ
በቀደሙት ንባቦች የተመለከትናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሰዎች ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ወይም በሌሎች ነገሮች ላይ ስለማድረግ ሲሆን፤ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ፍጥረትም ተስፋ እንዳለው ያስረዳናል። ይህ መንፈስን የሚያድስ መልካም እይታ ነው።
በአሁኑ ጊዜ ተፈጥሮአዊው አካባቢያችን በፍጥነት እያሽቆለቆለ መምጣቱን፣ የምድር ከመጠን በላይ መጎሳቆል እና የአየር ንብረት ለውጥ እየተሰቃየች ሲሆን፤ ይዋል ይደር እንጂ ይህ ሁኔታ እየባሰ ይሄዳል። በዙሪያችን እየተከናወኑ ያሉትን ሁኔታዎች እና ትንበያዎችን ከተመለከትን ሙሉ በሙሉ እርግጥ መሆኑን ያሳዩናል።
ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሰፋ ያለ ሌላ እይታ ይሰጠናል። በመጀመሪያ፣ የተፈጥሮ አደጋዎችና መከራዎች ከየት እንደመጡ ያሳያል፡- ''ፍጥረት ሁሉ ለከንቱነት ተዳርጓል፤ ይኸውም በራሱ ምርጫ ሳይሆን፣ ለተስፋ እንዲገዛ ካደረገው ከፈቃዱ የተነሣ ነው። ይህም ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ ነው። እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን'' (ሮሜ 8፡ 20-22)።
ኃጢአት ወደ እግዚአብሔር ፍጥረት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ፍጥረት የሀጥያትን ውጤት ተሸክምዋል። ኢየሱስ ሲመለስ ግን ይህ ይለወጣል! ኃጢአት በማይኖርበት ጊዜ ፍጥረት ከጥፋት ባርነት ነፃ ይወጣል።
ተስፋ አለ! ለሰው ብቻ ሳይሆን ለፍጥረትም ሁሉ ተስፋ አለ።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ለብዙ ሰዎች 'ተስፋ' አዎንታዊ ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው። አንድን ነገር ተስፋ ብናደርግም እንደሚሆን እርግጠኞች አይደለንም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እርግጠኛ እና እምነት የሚጣልበት የተስፋ ምንጭ እንዳለ ያስተምረናል። በዚህ የንባብ እቅድ 'እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ' ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር እንመለከታለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበ GlobalRize ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://www.globalrize.org/