ሮሜ 15:8-13

ሮሜ 15:8-13 NASV

ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ለእግዚአብሔር እውነት ሲል ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ እንደ ሆነ እነግራችኋለሁና፤ እንዲሁም አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ ያመሰግኑት ዘንድ ነው፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ።” ደግሞም፣ “አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ” ይላል። እንደ ገናም፣ “አሕዛብም ሁላችሁ ጌታን አመስግኑት፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወድሱት” ይላል። ኢሳይያስም እንዲሁ፣ “በሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚነግሠው፣ የእሴይ ሥር ይመጣል፤ በርሱም ሕዝቦች ተስፋ ያደርጋሉ” ይላል። በርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስስላችሁ ነው።