1
የማቴዎስ ወንጌል 6:33
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፥ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።
So sánh
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:33
2
የማቴዎስ ወንጌል 6:34
“ስለዚህ ስለነገ አትጨነቁ፥ ነገ ስለ ራሱ ይጨነቃልና፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:34
3
የማቴዎስ ወንጌል 6:25
ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ነፍስ ከምግብ ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:25
4
የማቴዎስ ወንጌል 6:6
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ በርህንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
ስለዚህ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን፤
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
6
የማቴዎስ ወንጌል 6:11
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:11
7
የማቴዎስ ወንጌል 6:12
እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:12
8
የማቴዎስ ወንጌል 6:13
ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:13
9
የማቴዎስ ወንጌል 6:14
የሰዎችን በደል ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ ይቅር ይላችኋል፤
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:14
10
የማቴዎስ ወንጌል 6:26
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም፥ ወይም አያጭዱም፥ ወደ ጎተራም አይሰበስቡም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል፤ ታዲያ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:26
11
የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
“ብልና ዝገት በሚያጠፉት፥ ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁበት በምድር ላይ ሃብት አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልና ዝገት በማያጠፉት፥ ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁበት በሰማይ ሃብትን ሰብስቡ፤ ሃብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይሆናልና።
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
12
የማቴዎስ ወንጌል 6:24
“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 6:30
ነገር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እግዚአብሔር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም?
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:30
14
የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4
አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ ይህም ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ነው። በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4
15
የማቴዎስ ወንጌል 6:1
“ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ መልካምም ሥራችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ዘንድ ሽልማት አታገኙም።
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:1
16
የማቴዎስ ወንጌል 6:16-18
“ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ሰዎች መጾማቸውን እንዲያዩላቸው ፊታቸውን ይለውጣሉና፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጾም፥ ራስህን ተቀባ፥ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር ላለው አባትህ እንጂ በሰዎች ዘንድ ጾመኛ ሆነህ እንዳትታይ፤ በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።
Khám phá የማቴዎስ ወንጌል 6:16-18
Trang chủ
Kinh Thánh
Kế hoạch
Video