የእግዚአብሔር የጦር ዕቃናሙና

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ

ቀን {{ቀን}} ከ8

በእግዚአብሔር ኃይል መዋጋት

"... በሁሉ ዐይነት ጸሎትና ልመና፣ በማንኛውም ሁኔታ በመንፈስ ጸልዩ’’ (ኤፌሶን 6:18)።

የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለው ከእግዚአብሔር ጋር ስንኖር ብቻ ነው። ከሁሉም በላይ የጦር ትጥቅ ነው፣ እሱ እራሱን ያቀርብልናል፤ የጦር ዕቃውን እንድንለብስ ያበረታታናል። የመንፈስን ሰይፍ ወይም የመዳንን ራስ ቁር ከጌታ መለየት አንችልም። በራሳችን ጥንካሬም ልንጠቀምባቸው አንችልም።

ከእግዚአብሔር ጋር የመገናኘት ዋና መንገድ ጸሎት ነው። ጳውሎስ “በሁሉም ጊዜ” እንድንጸልይ አበረታቶናል፣ ያም ማለት በሁሉም ተስማሚ አጋጣሚዎች፤ ጸሎት ለሚፈልጉ ነገሮች ሁሉ ማለት ነው። እነዚህ ጸሎቶች አምልኮን እና ኃጢአታችንን መናዘዝን ያካትታሉ፣ በተጨማሪም ለፍላጎታችን እና በዙሪያችን ላሉ ሌሎች ፍላጎቶች መጸለይን ያካትታሉ። የዘወትር የጸሎት ልማዶች፣ ከአምላክ ጋር ተቀራርበን መኖር እና ሁሉንም ነገር ከእርሱ ጋር መካፈል ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ያጠናክርልናል። በዚህ መንገድ፣ “የኃይሉን ብርታት” (ኤፌሶን 6፡10) እናገኛለን።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁል ጊዜ እንድንጸልይ እንዳንታክት ብዙ ምክሮችን እናነባለን (ሉቃስ 18፡1)፣ ሳታቋርጡ እንድትጸልዩ እና በማንኛውም ሁኔታ አመስግኑ (1ኛ ተሰሎንቄ 5፡17-18)። ኢየሱስም ብዙ ጊዜ በጸሎት ያሳልፍ ነበር።

ጤናማ የጸሎት ልምዶች አሎት?

ይህ የንባብ እቅድ እርስዎን እንዳበረታታ ተስፋ እናደርጋለን እናም በየቀኑ ከክርስቶስ ጋር የበለጠ ለመራመድ ፍላጎት እንዳለዎት ተስፋ እናደርጋለን።

ስለዚህ እቅድ

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ

ክርስቲያን ከሆንክ ያለማቋረጥ በጦርነት ላይ ነህ። በአካላዊ ጉዳት ስለተጠቃህ አይደለም፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ኃይሎች ከአምላክ ሊያርቁህ ስለሚሞክሩ ነው። አንተን ለመጠበቅ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ ይሰጥሃል። ይህ የንባብ እቅድ - የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ያብራራል።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ www.globalrize.org