የእግዚአብሔር የጦር ዕቃናሙና

የጽድቅ ስጦታ
"...የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ" (ኤፌሶን 6:14)
የደረት ጥሩር የአንድን ወታደር ልብን ይጠብቃል፤ ይህም በምሳሌያዊ አነጋገር ስሜቶች የሚኖሩበት የሰው የሕይወቱ ወሳኝ ስፍራ ነው።
ስለዚህ “የጽድቅ ጥሩር” ስሜታችንን ለመጠበቅ የሚጠቅመን ሲሆን፤ ብዙ ጊዜ ሰይጣን እኛን የሕይወት መንገድ ስሜታችንን በማወክ ወደ የማይሆን ሕይወት ሊመራን ይሞክራል። ሲሳካለትም ይታያል።
በአንድ በኩል፣ "እኛ በራሳችን ጽድቅ በመኩራራት እኔ ምን ያህል ጥሩ ክርስቲያን እንደሆንኩ ተመልከት፣ እግዚአብሔር በእርግጥ በእኔ ይደሰታል!" በሌላ በኩል፣ አንዳንዶች ኢየሱስ በእውነት እንዳዳናቸው ማመን ይከብዳቸው፤ "እኔ እንደዚህ ጎስቋላ ነኝ… እግዚአብሔር በእውነት ሊወደኝ ይችላል? በእውነት መዳኔን እርግጠኛ መሆን እችላለሁን?" ከእነዚህ አሳሳች ስሜቶች የሚያድነው የሚታደገው ጠበቃ የሆነው የክርስቶስ ጽድቅ ነው። መዳናችን በራሳችን ላይ ጽድቅ የተመሰረተ ሳይሆን እግዚአብሔር በእኛ ላይ በሚቆጥረው ጽድቅ ላይ ብቻ ነው! "እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው" (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21)። ማርቲን ሉተር ይህንን “ታላቅ ልውውጥ” በማለት ጠርቶታል፡ ኢየሱስ ኃጢአታችንን ይወስዳል፣ ጽድቁንም እንቀበላለን። ዲያብሎስ ምንም እንኳን ቢወተውታቸው - አማኞች ከእግዚአብሔር ፊት በትክክል መቆም የሚቸሉት በዚህ የጽድቅ እውቀት ነው።
የኢየሱስን ጽድቅ እንደ የእግዚአብሔር ነፃ ስጦታ ተቀብለሃል?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ክርስቲያን ከሆንክ ያለማቋረጥ በጦርነት ላይ ነህ። በአካላዊ ጉዳት ስለተጠቃህ አይደለም፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ኃይሎች ከአምላክ ሊያርቁህ ስለሚሞክሩ ነው። አንተን ለመጠበቅ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ ይሰጥሃል። ይህ የንባብ እቅድ - የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ያብራራል።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ www.globalrize.org