የእግዚአብሔር የጦር ዕቃናሙና

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ

ቀን {{ቀን}} ከ8

በእውነት ጸንቶ መኖር

"እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ዝናር ታጥቃችሁ" (ኤፌሶን 6:14)

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ የመጀመሪያው የምናየው "የእውነት መታጠቂያ" ነው። ቀበቶ በጦርነት ውስጥ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ለመረዳት የሮማውያን ወታደሮች ምን አይነት ልብሶችን እንደለበሱ ማወቅ አለብን። እነዚህ ልብሶች የአንድን ወታደር እንቅስቃሴ በጦርነት እንዳያደናቅፉት፤ በወገቡ ላይ ባለው ቀበቶ ታስረዋል። ቀበቶ ከሌለ አንድ ሰው በቀላሉ ሊሰናከል ይችላል - ይህ በጦርነት ውስጥ በጣም ወሳኝ ነው።

በተመሳሳይም እውነትን የማያውቁ ክርስቲያኖች በቀላሉ "ሊሰናከሉ" ይችላሉ። “የሐሰት አባት” ተብሎ በሚጠራው ሰይጣን በቀላሉ ያታልላቸዋል (ዮሐንስ 8:44)፤ የሐሰት ትምህርት እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል። ከዚህም በላይ እነዚህ አማኞች ስለ እግዚአብሔር እና ስለ መንፈሳዊ ሕይወት ጥቂት ስለሚያውቁ በመከራ ጊዜ በቀላሉ ወደ ኋላ ይመለሳሉ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጸው የእግዚአብሔርን እውነት ማወቅ እና መረዳት ለአንድ ክርስቲያን መሠረታዊ ጠቀሜታ አለው። በዮሐንስ 8 ላይ ኢየሱስ “በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል” ብሏል።

በእውነት መታጠቂያ ታጥቀሃል?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ስለዚህ እቅድ

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ

ክርስቲያን ከሆንክ ያለማቋረጥ በጦርነት ላይ ነህ። በአካላዊ ጉዳት ስለተጠቃህ አይደለም፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ኃይሎች ከአምላክ ሊያርቁህ ስለሚሞክሩ ነው። አንተን ለመጠበቅ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ ይሰጥሃል። ይህ የንባብ እቅድ - የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ያብራራል።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ www.globalrize.org