የእግዚአብሔር የጦር ዕቃናሙና

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ
‘’የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ መቋቋም ትችሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ’’
( ኤፌሶን 6:11 )።
ጳውሎስ ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን በጻፈው ደብዳቤ መጨረሻ ላይ አንባቢዎቹን "የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ እንዲለብሱ" አሳስቧቸዋል። አካላዊ ጉዳት ስለተጠቁ ሳይሆን፤ የክርስቲያን ሕይወት ከእግዚአብሔር ሊያርቁን በሚሞክሩ በሰይጣንና በአገልጋዮቹ የማያቋርጥ መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ስለሆንን ነው። ከእነዚህ ክፉ መንፈሳዊ ኃይሎች ተንኮል እኛን ለመጠበቅ፤ የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ እጅግ አስፈላጊ ነው።
ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ ጠላቶች ላይ፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ኃይል ያስፈልገናል። ስለዚህም ጳውሎስ አንባቢዎቹን ‘’በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ’’ (ቁጥር 10) ላይ በምክሩን አሳስቧቸዋል። ጌታ ኢየሱስ ብቻ ሰይጣንን የማሸነፍ ሥልጣን አለው፡- ‘’የገዦችና የባለሥልጣናትንም ማዕርግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ’’ ( ቆላስይስ 2፡15)።
ክርስቶስ ለአማኞች መንፈሳዊ የጦር ትጥቆችን ይሰጣል፣ እነሱም እራሳቸውን ለመጠበቅ ሊለብሱት ይገባል። በሚቀጥሉት ቀናት ይህን የጦር ትጥቅ አንድ በአንድ እንወያያለን፤ እንዲሁም ጳውሎስ ስለእነዚህ በጦር ትጥቆች ያስተማረውን ትምህርቶች እንመልከታለን።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ክርስቲያን ከሆንክ ያለማቋረጥ በጦርነት ላይ ነህ። በአካላዊ ጉዳት ስለተጠቃህ አይደለም፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ኃይሎች ከአምላክ ሊያርቁህ ስለሚሞክሩ ነው። አንተን ለመጠበቅ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ ይሰጥሃል። ይህ የንባብ እቅድ - የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ያብራራል።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ www.globalrize.org