የእግዚአብሔር የጦር ዕቃናሙና

ወንጌል ለሁሉም የሕይወት ክፍላችን ሁሉ ብቂ ነው
"...በሰላም ወንጌል ዝግጁነት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ’’ (ኤፌሶን 6:15)።
እግሮቻችን በርትቶ መቆም በጣም አስፈላጊ እና ዋና ነው። በተመሳሳይም በእምነት ጸንቶ መቆም የሚቻለው ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ባገኘህበት በወንጌል ብቻ ነው። በጌታ መንገድ ለመጓዝ እና በወንጌሉ መሰረት ለመኖር ነቅተህ ውሳኔ ካደረግክ፣ ትክክለኛ ቦታህን መያዝ ትችላለህ።
ይህ የሰላም ወንጌል ከሌለህ ለሌሎች ትችት የተጋለጥክ እና ከነሱ አመለካከት ወይም መመሪያ ጋር ለመስማማት ትጥራለህ። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ደንቦችህና እሴቶችህ የሌሎችን ስሜት ሊጎዱ እንደሚችሉ ትፈራ ይሆናል፤ ወይም በእምነትህ ታፍራለህ ወይም ይህ ስራህን ሊያደናቅፍ ይችላል ብለህ ትጨነቃለህ። ለመስማማት ታመነታለህ፣ ቀስ በቀስ ግን በእርግጠኝነት ከዘላለማዊ ህይወት መንገድ ትሸሻለህ።
ክርስቲያኖች ጸንተው መቆም የሚችሉት "በሰላም ወንጌል የተሰጠውን ዝግጁነት ከለበሱ" ብቻ ነው። ይህ ወንጌል ሊመጡ የሚችሉትን ችግሮች እና ኃላፊነቶች ጨምሮ ለሁሉም ነገር ዋጋ እና ብቃት ያለው መሆኑን እርግጠኞች መሆን አለባቸው።
በሰላም ወንጌል ዝግጁነት እግሮቻችሁ ተጫምተዋል?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ክርስቲያን ከሆንክ ያለማቋረጥ በጦርነት ላይ ነህ። በአካላዊ ጉዳት ስለተጠቃህ አይደለም፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ኃይሎች ከአምላክ ሊያርቁህ ስለሚሞክሩ ነው። አንተን ለመጠበቅ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ ይሰጥሃል። ይህ የንባብ እቅድ - የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ያብራራል።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ www.globalrize.org