የእግዚአብሔር የጦር ዕቃናሙና

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ

ቀን {{ቀን}} ከ8

ጥበቃ የሚገኝበት እምነት

‘’የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ’’ (ኤፌሶን 6:16)።

ሰይጣን በጣም እውን ነው፣ ጥቃቶቹም እውን ናቸው። የሚቃጠሉ ፍላጻዎች ጋር ይነጻጸራሉ፣ እኛን ለመጉዳት እና ለአዳኛችን እና ለጌታችን ያለንን ፍቅር እና ቅንዓት እንድናጣ ያደርገናል። ነገር ግን እነዚህን የሚንበለበሉትን ፍላጻዎች ልናጠፋው የምንችልበት በእምነት ጋሻ እግዚአብሔር ይጠብቀናል።

ዲያብሎስ በጣም ጨካኝ ነው። በቀጥታም ሆነ በዙርያችን ባሉ ሰዎች ያጠቃናል። ጳውሎስ ከተሞክሮ፣ ሲታሰር እና ሲሰቃይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪም ጥቃት እንደደረሰበት በግልጽ እናያለን፤ ለምሳሌ በ2 ጢሞቴዎስ 1 እንደምናየው ...በሚያልፍበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ብዙ አማኞች ከእርሱ እንደራቁት ጉዳቱን እንመለከታለን።

የእምነት ጋሻ በሁለት መንገድ ይረዳል፡ የዲያብሎስን ክፉ ጥቃት እንድናይ ያስችለናል እንዲሁም ከሰይጣን የሚበልጠውን የአምላካችንን መጠጊያ አጥብቀን እንድንፈልግ ይረዳናል ። "ከአቅማችሁ በላይ እንድትፈተኑ አይፈቅድም ነገር ግን እንድትታገሡት ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያዘጋጃል" (1ኛ ቆሮንቶስ 10:13)።

የሰይጣንን ጥቃት ውስጥ ነህ? እራስህን ለመጠበቅ የእምነትን ጋሻ ትጠቀማለህ?

ስለዚህ እቅድ

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ

ክርስቲያን ከሆንክ ያለማቋረጥ በጦርነት ላይ ነህ። በአካላዊ ጉዳት ስለተጠቃህ አይደለም፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ኃይሎች ከአምላክ ሊያርቁህ ስለሚሞክሩ ነው። አንተን ለመጠበቅ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ ይሰጥሃል። ይህ የንባብ እቅድ - የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ያብራራል።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ www.globalrize.org