በእምነት መኖርSample

የክፉው ቀን
“… ሁሉንም ነገር ከፈፀማችሁ በኋላ ፀንታችሁ መቆም ትችላላችሁና…”
መንፈሳዊ ትጥቃችን ለበረከት ቀን ሳይሆን ለክፉ ቀን እንደሚያዘጋጀን እዚህ ላይ ልብ ይበሉ፡፡ በተጨማሪም “የክፉው ቀን ቢመጣ” ሳይሆን “የክፉው ቀን ሲመጣ” እንደሚልም ያስተውሉ። እውነተኛ ማንነታችንን የሚገለጠው የበረከት ቀን ሳይሆን የክፉ ቀን ላይ ነው፡፡ የእስራኤል ልጆች ቀይ ባሕርን እስኪሻገሩ ድረስ ደህና ነበሩ፣ ከሦስት ቀናት በኋላ ግን በማራ ውሃ እውነተኛ ማንነታቸው ተገለጠ፡፡ (ዘፀ 15: 24) አሥሩ ሰላዮች ከተስፋይቱ ምድር አስደንጋጭ ዜና ይዘው እስኪመለሱ ድረስ ሁሉም መልካም መስለው ነበር፡፡ (ዘኁ.14:1) ይህን ስላቹ አሉታዊ ንግግርን እየደገፍኩ አይደለም፣ እንዲያውም አዎንታዊ ቃል ማውጣትን አበረታታለሁ፡፡ ክፉ ቀን የእምነት ቃላችሁን ወደ ስንፍና ቃል ከለወጠው፣ ከመጀመሪያውኑ አዎንታዊ የሆነ የእምነት ቃል በጭራሽ አልነበራችሁም ማለት ነው፡፡
ትጥቃችን ለመዋጋት ሳይሆን በክፉ ቀን ለመቆም ያዘጋጀናል፡፡ በዚህ ዓለም ተቃዋሚዎቻችንን እንታገላለን፣ በመንፈሳዊው ዓለም ግን ትግላችንን የምናደርገው ፀንተን በመቆም ነው፡፡ በመንፈሳዊ አቋም መቆምና በአካል መቆም የተለያዩ መሆናቸውን መረዳት አለብን ፡፡ በመንፈሳዊው መቆም ማለት እግዚአብሔር የሰጠንን ተስፋዎች በመጠባበቅ በእምነት ፀንቶ መቆም ነው፡፡ የአምልኮ ቡድኑ የምንወደውን መዝሙር በሚዘምርበት ጊዜ መነቃቃት ብቻ ሳይሆን በክፉ ቀን ስናልፍም ሆነ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች ሲዘገዩ ወይም የቀሩ ሲመስል የሰጠንን ተስፋዎች በእምነት መጠባበቅ ማለት ነው፡፡ በአካላዊ ውጊያ ውስጥ መቆም ሊያስጠቃን ይችላል፡፡ ነገር ግን በመንፈሳዊው ውጊያ በመንፈስ መቆም ድል ነው፡፡
“በለቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል…” መዝ.84: 6
የሕይወት ተዛምዶ
በክፉ ቀን ለክፉ ቀን መዘጋጀት በጣም የዘገየ እንደሆነ ያስታውሱ። ስፖርት ቤት ውስጥ ሰውነትዎን እንደሚያጠነክሩ ሁሉ መንፈስዎን በየቀኑ እንዲያዳብሩ አበረታታዎታለሁ፡፡ እኔ በግሌ በየቀኑ የመገናኛው ድንኳን ፀሎት ተብሎ የሚጠራውን የፀሎት አይነት እጠቀማለሁ ፡፡ በመንፈሳዊ ህይወቴ ውስጥ እጅግ ጠቃሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ፡፡
ፀሎት
አባት ሆይ፣ ስለማይለወጥ እና ስለማይሻሩ ተስፋዎችህ አመሰግንሃለሁ፡፡ ዛሬ ከአንተ ጋር እቆማለሁ!
Scripture
About this Plan

በእምነት ለመቆም፣ በእምነት የተሞሉ ፀሎቶችን ለመጸለይ እና በሕይወትዎና በሌሎችም ሕይወት ውስጥ ለመንግሥቱ አስገራሚ ነገሮችን ለማከናወን እግዚአብሔር ሊጠቀምብዎት ይችላል። የሚቅጥሉትን 5 ቀናት ይህን እምነቶን በማሳደግ ያሳልፉ።
More
Related Plans

Whatsoever You Do In Word or Deed

Living in the Light

Kingdom Come

Discover the New Door!

Imperfect Dads, One Perfect Father

Tranformation: Jesus Tranforms You

Transformed by Christ: Lives of the Apostles

How Is It With Your Soul?

House of David, Season 2: Trusting God in the Middle of the Story
