በእምነት መኖርSample

የራሳችሁን ቃል አክብሩ
'“አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ እኛም በዚያው የእምነት መንፈስ እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን፡፡' 2 ቆሮንቶስ 4:13
ቃላቶቻችንን የተገባቸውን አክብሮት ብንሰጣቸው ምንኛ ድንቅ ነበር፡፡ አባታችን ድምፃችንን እንዴት በፍቅር እንደሚጠብቅ ብንረዳ የማይመለሱ የሚመስሉ ፀሎቶች ምንኛ በተዓምራዊ መንገድ በተመለሱ፡፡ እርሱ በመጀመሪያ ጊዜ የሚሰማ አምላክ ነውና፡፡ መለመን አያስፈልግም፡፡ ማመን ብቻ!
ደጋግማችሁ የምትፀልዩዋቸው ፀሎቶች በጥርጣሬ ሳይሆን በእምነት ወደ አብ እንደምታሳርጉ አስተውሉ። እንደተሰማን ከተጠራጠርን ወይ የእርሱን የመስማት ችሎታ እንጠራጠራለን ወይ ደግሞ ልጅነታችንን ጥያቄ ውስጥ እናስገባዋለን - ሁለቱም ትርጉም የለሽ ናቸው! የጉዲፈቻ አስተሳሰብ ገስፃችሁ በአባታችሁ ቤት በመኖራችሁ ደስ ይበላችሁ!
እግዚአብሔር ቃላቶቻችን እንደ እርሱ ቃላት ክብደት እንዲኖራቸው ይፈልጋል፡፡ “እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያንጸባረቅን፣ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።” (2ኛ ቆሮ 3:18) እንደ ልጆቹ እጣ ፈንታችን ይህ ነው። ዛሬ የራሳችሁን ፀሎት በማክበር ተጠቀሙ። አንድ ጊዜ ፀልዩ፣ ከዚያም ሳትጠራጠሩ እመኑ። አንድ ጊዜ ፀልዩና በድርጊታችሁም ግለፁት። ኃያል ነገር ነው፡፡ ሕንፃውን በደንብ ያያዘውን ሚስማር ደጋግሞ በሞደሻ መምታት አያስፈልግም። ግን እንደገና ስትፀልዩ፣ በመጀመሪያውን ፀሎት መሰማት በእምነት ላይ ቆማችሁ፣ በሁሉን ቻይ እጆቹ እምነታችሁን አውጁ፡፡
የሕይወት ተዛምዶ
እግዚአብሔርን ስትለምን ራስህን አግኝተኸው ታውቃለህ? ያንን ገልብጡትና የእግዚአብሔር ልጅነታችሁን ማወጅ ጀምሩ።
ፀሎት
ኢየሱስ ሆይ፣ የራሴን ቃል ባለማክበሬ ይቅር በለኝ፡፡ በሚገባ እንደምትሰማኝና ስልጣንን ወደ አንደበቴ የምትመልስ አምላክ እንደሆንክ ያለኝን ጽኑ እምነት እገልጻለሁ፡፡ አመሰግንሃለሁ፡፡ አሜን!
Scripture
About this Plan

በእምነት ለመቆም፣ በእምነት የተሞሉ ፀሎቶችን ለመጸለይ እና በሕይወትዎና በሌሎችም ሕይወት ውስጥ ለመንግሥቱ አስገራሚ ነገሮችን ለማከናወን እግዚአብሔር ሊጠቀምብዎት ይችላል። የሚቅጥሉትን 5 ቀናት ይህን እምነቶን በማሳደግ ያሳልፉ።
More
Related Plans

Whatsoever You Do In Word or Deed

Living in the Light

Kingdom Come

Discover the New Door!

Imperfect Dads, One Perfect Father

Tranformation: Jesus Tranforms You

Transformed by Christ: Lives of the Apostles

How Is It With Your Soul?

House of David, Season 2: Trusting God in the Middle of the Story
