YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 111

111
መዝሙር 111#111 የግጥሙ መሥመሮች እያንዳንዳቸው ከላይ እስከ ታች በተከታታይ በዕብራይስጥ ፊደሎች ቅደም ተከተል የተቀመጡ ናቸው።
1ሃሌ ሉያ።
በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣
እግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።
2እግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፤
ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።
3ሥራው ባለክብርና ባለግርማ ነው፤
ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
4ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤
እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው።
5ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤
ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።
6ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣
የአሠራሩን ብርታት አሳይቷል።
7የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው፤
ሥርዐቱም ሁሉ የታመነ ነው፤
8ከዘላለም እስከ ለዘላለም የጸና ነው፤
በእውነትና በቅንነትም የተሠራ ነው።
9ለሕዝቡ መዳንን ሰደደ፤
ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤
ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው።
10 እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤
ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤
ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።

Currently Selected:

መዝሙር 111: NASV

Highlight

Copy

Compare

Share

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in