YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 110

110
መዝሙር 110
የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ጌታዬን፣
“ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ፣
እስከማደርግልህ ድረስ፣
በቀኜ ተቀመጥ” አለው።
2 እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰድዳል፤
“አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።”
3ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣
ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤
ከንጋት ማሕፀን፣
በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣
የጕልማሳነትህን ልምላሜ#110፥3 ወይም ጕልማሶችህ እንደ ንጋት ወዳንተ ይመጣሉ ማለት ነው። እንደ ጠል ትቀበላለህ።
4“እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት፤
አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣
እግዚአብሔር ምሏል፤
እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።
5ጌታ በቀኝህ ነው፤
በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቅቃቸዋል።
6በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤
በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል።
7መንገድ#110፥7 ወይም ሥልጣን ለመስጠት ኀይል ያለው ሥልጣን ላይ ያስቀምጠዋል ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል፤
ስለዚህ ራሱን ቀና ያደርጋል።

Currently Selected:

መዝሙር 110: NASV

Highlight

Copy

Compare

Share

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in