YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 112

112
መዝሙር 112
1ሃሌ ሉያ።#112፥1 እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ነው።
ብፁዕ ነው፤
እግዚአብሔርን የሚፈራ፣
በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ፤
2ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤
የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤
ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።
4ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣
ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
5ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣
ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል።
6ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤
ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል።
7ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤
ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።
8ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤
በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
9በልግስና ለድኾች ሰጠ፤
ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤
ቀንዱም#112፥9 በዚህ ስፍራ ክብርን ያመለክታል። በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10ክፉ ሰው ይህን በማየት ይበሳጫል፤
ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፤
የክፉዎችም ምኞት ትጠፋለች።

Currently Selected:

መዝሙር 112: NASV

Highlight

Copy

Compare

Share

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in