መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?ናሙና

አትኩሮትህን በኢየሱስ ላይ አድርግ።
"ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? … አይደለም፣ በእነዚህ ሁሉ ነገሮች በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ( ሮሜ 8:35-37 )
በኢየሱስ ደም የዳነ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ከፍቅሩ ምንም ሊለይህ አይችልም። ሞትም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን... ከቶ ምንም የለም። መከራ፣ ጭንቀት እና ስደት እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር እየቀነሰ ለመሆኑ ምክንያትም ማስረጃም አይደሉም። ጳውሎስ ለኢየሱስ ሲል በታሰረበት ወቅት እንዳጋጠመው ሌሎች ሰዎችም ከእኛ ሊርቁ ይችላሉ። ጌታ ግን አይርቅም። እኛን መውደዱን አያቆምም።
ከኢየሱስ ጋር የተገናኘህ ስለሆነ በሞት፣ በሰይጣን እና በሁሉም ነገር ላይ ባደረገው ድል ትካፈላለህ። በጦርነቱ መካከል ድል አለህ። ስለ እምነትህ ብትገደል እንኳ "ከአሸናፊው በላይ" ነህ። በእውነቱ፣ ክርስቶስ ጠላቶቹን በተመሳሳይ መንገድ ድል ነስቶታል - በመስቀል ላይ በመሞት! በእርሱ የኃጢያት ክፍያ እዳህ ተሰርዮልሃል። ስለዚህ ሰይጣን ከእንግዲህ በአንተ ላይ የይገባኛል ጥያቄ የለውም። በበጉ በኢየሱስ ደም ልታሸንፈው ትችላለህ (ራዕይ 12፡9-11 ተመልከት)። ስለዚህ፣ መከራን በምትጋፈጥበት ጊዜም ቢሆን፣ ከእግዚአብሄር ሃሳብ ጎን ከሆንህ፣ በአሸናፊው ማህበር ውስጥ ነህ።
የድካም ስሜት ከተሰማህ፣ ሮሜ 8ን አንብብ። አትኩሮትህን በድል አድራጊው ንጉሥህ ኢየሱስ ላይ አድርግ!"
አሁን ይህንን የንባብ እቅድ ጨርሰዋል። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ መማር ከፈለጉ፣ የእኛን ኢ-ኮርስ የኢየሱስ ሕይወት መመዝገብ ይችላሉ። ለመልስዎ ግብረ መልስ የሚሰጥ እና ተከታይ ጥያቄዎችን የሚጠይቅ የግል አማካሪ ይኖርዎታል።
ስለዚህ እቅድ

ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org