መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?ናሙና

ጳውሎስ የወንጌልን መስፋፋት ከራሱ ሕይወት የበለጠ አስፈላጊ አድርጎ ይመለከተው ነበር።
“መንፈስ ቅዱስ እስራትና መከራ ይቆይሃል ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል። ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ” ( የሐዋርያት ሥራ 20:23-24 )።
በሐዋርያት ሥራ 9፡15-16 እግዚአብሔር ስለ ጳውሎስ ሲናገር፡- “ይህ ሰው ለአሕዛብና ለነገሥታቶቻቸው ለእስራኤልም ሕዝብ ስሜን እሰብክ ዘንድ የመረጥሁት ዕቃ ነው። ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው አሳየዋለሁ” አለ። ከብዙ ዓመታት በኋላ ጳውሎስ ብዙ መከራ ደርሶበታል፤ መከራዎች እንደሚጠብቁት ያውቃል። እንደሚታሰር መንፈስ ቅዱስ ስለመሰከረ ሌሎች ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ገፋፉት። ሆኖም ጳውሎስ ተልዕኮውን ለመቀጠል ቆርጦ ነበር። ለወዳጆቹ “ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም ልታሰር ብቻ ሳይሆን በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ዝግጁ ነኝ” (ሐዋ. 21፡13) አላቸው።
የጳውሎስ የሚስዮናዊነት ሥራውን ትቶ ቢሆን ኑሮው ቀላል እና የበለጠ ምቹ ሊሆን ይችል ነበር። ነገር ግን ጳውሎስ፣ ጌታ ኢየሱስ እንዲሠራው የሰጠውን ሥራ መጨረስ መከራው ዋጋ እንዳለው ተናግሯል። ወንጌልን ማካፈል በጣም አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ ጳውሎስ ህይወቱን ለዚያ ለመስጠት ዝግጁ ነበር። ለታማኝ አገልግሎቱ እግዚአብሔር አብዝቶ እንደሚከፍለው እርግጠኛ ነበር (2 ጢሞቴዎስ 4፡7-8 ተመልከት)።
ለወንጌል መስፋፋት መስዋእት ለመክፈል ዝግጁ ናችሁ?
ስለዚህ እቅድ

ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org