መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?ናሙና

መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ18

መከራ የክርስቲያኖች የሕይወት ክፍል ነው።

የደቀ መዛሙርቱንም ልብ በማበረታታትና በእምነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ በመምከር፣ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ማለፍ አለብን” አሏቸው ( የሐዋርያት ስራ 14:22)። ሐዋርያው ጳውሎስ ብዙ ይጓዝ ነበር። ወንጌልን ለማስፋፋት ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ሄደ። በሐዋርያት ስራ 14 እንደምንመለከተው ብዙ ፍሬ አፍርቷል፣ ነገር ግን ተቃውሞም ይገጥመው ነበር። በመጨረሻም ጳውሎስና በርናባስ ሰዎች ሊወግሯቸው ስለሞከሩ ከተማዋን ለቀው ወጡ።

በሚቀጥለው ከተማ በልስጥራ ጳውሎስ በድንጋይ ተወግሮ ነበር። ሰዎቹ የገደሉት መስሏቸው ከከተማው ውጭ አወጡት። ጳውሎስ ግን አልሞተም ነበር፤ ወደ ሌላ ቦታ ወንጌልንም መስበክ ቀጠለ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በዚያ የሚኖሩትን አማኞች ሕይወት ለማጽናት ወደ ልስጥራና ወደ ኢቆንዮን - ሰዎች ሊገድሉት ወደ ሞከሩባቸው ከተሞች ተመለሰ። እነዚህ ሰዎች ዜጎቻቸው ለጳውሎስ ያላቸውን ጥላቻ ሲመለከቱ ወደ እምነት የመጡት እምብዛም አልነበረም። ክርስቲያን መሆን ከባድ እና አደገኛ ነበር! ጳውሎስና በርናባስ ግን “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ይገባናል እያሉ” በእምነት እንዲቀጥሉ አበረታቷቸዋል (ሐዋ. 14፡22)።

እነዚህ ሰዎች ለክርስቶስ ሲሉ መከራ መቀበላቸው እውነት ነበር። ጳውሎስ እንዲህ ያሉ መከራዎች ለክርስቲያኖች 'የተለመዱ' እንደሆኑ ተናግሯል። ይህ አባባል ያበረታታሃል ወይስ ያስጨንቅሃል?

ስለዚህ እቅድ

መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?

ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org