መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?ናሙና

መከራ መልካም ነገርን ያመጣል።
"መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን" ( ሮሜ 5:3-4 )።
በመከራዎች መካከል ደስታን ማግኘት እንደሚቻል አስቀድመን ተምረናል፣ መንፈስ ቅዱስ አማኞችን በሚያጋጥማቸው ነገር ሁሉ ከተፈጥሮ በላይ በሆነ ደስታ ሲሞላ። በዛሬው ጥቅስ ላይ፣ ጳውሎስ ባጋጠመው ችግር እንኳን ደስ ብሎኛል ብሏል። ለዚህ አስደናቂ አስተያየትም ምክንያቱን ይጠቅሳል። በደረሰበት ሥቃይ የሚደሰተው ስቃዩ ታላቅ እንደሆነ ስለሚሰማው ሳይሆን ስቃዩ እምነቱን እንደሚያጠናክር ስለሚያውቅ ነው።
ሐዋርያው ያዕቆብም ስለ ፈተናዎች ሲናገር፡- “ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ጽናትን እንዲያደርግላችሁ ታውቃላችሁና እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት። እነዚህ ሰዎች እንደ ጽናትና ትዕግስት ያሉትን መልካም ባሕርያት ማዳበራቸው በጣም አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሣ መከራ መቀበል ነበረባቸው። እነዚህ ሰዎች 'ፍጹምና ሁሉን ያሟሉ፣ አንዳችም የማይጎድላቸው' ለመሆን ይጥሩ ነበር። ( ያዕቆብ 1:4)
ኢየሱስ በሚመለስበት ጊዜ ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ወደ ፍፁምነት ይደርሳሉ። እስከዚያ ድረስ፤ ውድቀቶች እና ድክመቶች እና ጉድለቶች ይኖራቸዋል። ነገር ግን፣ በመከራ ውስጥ ስታልፉ የራሳችሁ ባሕርይ ቀስ በቀስ ክርስቶስን ወደ መምሰል ሲለወጥ ማየት ለደስታ ትልቅ ምክንያት ነው።
ክርስቲያን ከሆንክ ጀምሮ ተለውጠሃል? ከየትኛው አንፃር?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org