መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?ናሙና

በእግዚአብሔር ኃይል ጸንቶ መኖር
"ኃይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን እችላለሁ።" ( ፊልጵስዩስ 4:13 )
በመዝሙር 23 ላይ ዳዊት ራሱን ከደካማ በግ ጋር ራሱን አመሳስሏል። በራሱ አቅም በሕይወት መኖር አይችልም። በራሱ፣ እሱ መኖር እንደማይችል፣ነገር ግን በእረኛው እንክብካቤ ፍጹም ደህንነት ውስጥ እንደሆነ ይገልጿል። በምሳሌያዊ አነጋገር “በሞት ጥላ” ተብሎ በሚጠራው በጣም ጨለማ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን፣ እግዚአብሔር የሚያበረታው እና የሚጠብቀው ስለሆነ በማንኛውንም አደጋ በእግዚአብሔር ይታመን ነበር።
ጳውሎስም በራሱ አቅም መሸከም ያልቻለውን ብዙ መከራ ውስጥ አልፏል። እርሱ ግን “በሚበረታኝ በእርሱ” - በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል ጸንቷል። በእምነቱም ታስሮ ባልንጀሮቹ በተውት ጊዜ “ጌታ ከጎኔ ቆሞ አበረታኝ” በማለት ጳውሎስ ይመሰክራል (2 ጢሞቴዎስ 4፡17)።
ኢየሱስ የማይቀረውን ስቃይና ሞት በተጋፈጠበት ወቅት፣ በጣም ተጨነቀ። የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኑ የአብን ቁጣ መታገስ ቀላል አልነበረም! በመከራውም ጸለየ። እግዚአብሔርም ያበረታው ዘንድ መልአኩን ከሰማይ ላከ።
ስለዚህ ከዚህ ሁሉ ልናስተውል የሚገባው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ ጥንካሬ መጽናት ካልቻለ፣ አኛም በራሳችን ሃይል መሞከር እንኳን አይገባንም። ጭንቀትህን ሁሉ ለእግዚአብሔር ስጥ፤ እርሱም ያበረታሃል ።
ስለዚህ እቅድ

ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org