Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?Sample

እግዚአብሔር የመጨረሻ ቃል አለው
የሐጌ መጽሐፍ ጭብት መልዕክት የሚያሳየው የአምልኮ ትልቁ መገለጫው ከተሸነፈ ልብ ለእግዚአብሔር መታዘዝን ነው፡፡ ሐጌ የእግዚአብሔር ህዝብ በልባቸው ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን የስልጣን ባለመብትነት እንደገና እንዲመልሱና ወደ እውነተኛው አምልኮ እንዲመለሱ ይጠራቸዋል፡፡ የምታመልከው በልብህ ላይ ኃይልን ያደርጋል፤ እንዲሁም በህይወትህ ላይ፡፡ እኔና አንተ ወደ ኃጢአት የሚወስደውን መንገድ ከመጠን በላይ ቅድሚያ የምንሰጥ፤ ሲያልፍም ከእግዚአብሔር ውጪ ያሉትን ጣኦታችን አድርገን የምናመልክ አይደለን? ስለዚህ እግዚአብሔርን የልባችን ማዕከል ለማድረግና በህይወታችን ኃጢአትን ለመዋጋት ተግባራዊ የሆነ እርምጃ መውሰድ ያስፈልገናል፡፡ ሐጌ ህዝበ ለእስራኤል እግዚአብሔር ብቻ መመለክ እንዳለበትና እግዚአብሔር ብቻ በህይወታችን ስልጣን እንዳለው ያሳስባል። የመጨረሻ የሚላቸው አለው፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ከስደት እንደተመለሱ ነው፤ በሐጌ ግልጽ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ምስል ውስጥ ለተገለጹት የእግዚአብሔር መግለጫዎችና ተስፋዎች በልዩ ሁኔታ ያበረታቸው ነበር።
በሐጌ በኩል ለዘሩባቤል የተላለፈው መልዕክት ዛሬም ለእኛ ይናገራል፡፡ ምናልባት የጦርነት ልምድ ፈፅሞ ላይኖረን ይችላል፤ ነገር ግን በመንፈሳዊ ዓለም ከዓለም ጋር፣ ከስጋ ጋር እና ከሰይጣን ጋር ጦርነት ውስጥ ነን፤ እግዚአብሔር ደግሞ እርሱ በሁሉም ሀይል፣ ስርዓተ-መንግስት እና መንግስት ላይ ከዚህ በፊት እንደ እርሱ ያልነበረ ወደፊትም የማይኖር ታላቅ ሉዓላዊ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ ሁሉም በመጨረሻው በታላቁ ስልጣንና ፍርድ ስር ይመጣሉ። ህይወትህን የተቆጣጠረው ጦርነት አሁን ድረስ ምንም እንኳን የማያባራ፣ የሚያደክም እና የሚያስጨንቅ ቢሆንም፣ አንድ እውነት ግን ተረዳ እግዚአብሔር አንተን የሚያበረታታና ተስፋ የሚያሰንቅ የመጨረሻ ቃል እንዳለው። አንድ ቀን እግዚአብሔር በሁሉን ቻይነቱ የሚቃወሙትን ሁሉ ያጠፋቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ ቅዱስ እና ጻድቅ ነው።
እግዚአብሔር በሐጌ በኩል አምልኮን በቤተ መቅደስ ውስጥ በታማኝነት እንዲመልስ ከዳዊት ትውልድ ዘሩባቤልን እንደመረጠ ሲያወጅ እናያለን፡፡ እግዚአብሔር ዘሩባቤልን የክብር ሥልጣንና የባለቤትነት ማኅተም ቀለበት ምልክት ያደርገዋል፡፡ እግዚአብሔር ከሁሉም ህዝብ ለይቶ የራሱ ህዝብ መሆኑንና እንደገና በእነርሱ ላይ ባለስልጣን ስለመሆኑ ዘሩባቤልን ተጠቅሞ ትልቅ ሚና ሲጫወት እናያለን፡፡ ዘሩባቤል ዛሬ ላይ በሰፊው የሚታወስ ወይም የሚነገርለት አይደለም፤ ነገር ግን ከዳዊት ዘር የሆነ አንድ ሰው፤ እግዚአብሔር በሐጌ ትንቢት እያመለከ ያለው እርሱ ኢየሱስ ነው። የቤተ መቅደሱ እንደገና መገንባት እግዚአብሔር በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ ዳግም በእውነትና በመንፈስ እንዲያመልኩት ላዘጋጀው መንገድ ጥላ ነበር፡፡ በክርስቶስ እኛ ከእግዚአብሔር አባት ስልጣን ስር ሆነናል፡፡ ይህ የማንበብ ዕቅድ ወደ እርሱ የሚያቀርበን ነው፤ ነገር ግን ጉዞህ ወደ “ቀጣዩ ምንድነው” በርግጥ ጀምሯል፡፡ እግዚአብሔርን ለመታመን ለራስህ አንድ ነገር አስታውስ ይኸውም በነገር ሁሉ እርሱን ማስቀደም፣ ቅድስናን መከታተልና ህይወትህን ጨምሮ በሁሉ ነገሮችህ የመጨረሻ ቃል ያለውን አስደናቂ እውነት ማክበር፡፡
Scripture
About this Plan

ነገህን እየፈራህ ከሆነ ይህ የአምስት ቀናት እቅድ ለአንተ ነው፡፡ ምናልባት ልትቋቋመው የማትችለው አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞህ ይሆናል፤ ነገር ግን በአንድ ነገር እርግጠኛ ሆነህ ኑር ይኸውም በአንተ ሕይወት የመጨረሻው ቃል ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡ አግዚአብሐርን ማስቀደም፣ ህወትህን ከዓላማው ጋር ማጣጣም፤ በሚያጠነክርህና ቀጣዩ ምን እንደሆነ በሚያስቀጥልህ እውነት ላይ ማረፍን ተማር፡፡
More
Related Plans

The Lies We Believe: Beyond Quick Fixes to Real Freedom Part 2

Breath & Blueprint: Your Creative Awakening

Let Us Pray

Unapologetically Sold Out: 7 Days of Prayers for Millennials to Live Whole-Heartedly Committed to Jesus Christ

FruitFULL - Faithfulness, Gentleness, and Self-Control - the Mature Expression of Faith

Homesick for Heaven

Ruth | Chapter Summaries + Study Questions

Faith in Hard Times

Judges | Chapter Summaries + Study Questions
