1
ኦሪት ዘፍጥረት 28:15
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፥ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”
ប្រៀបធៀប
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:15
2
ኦሪት ዘፍጥረት 28:13
እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ፦ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፥
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:13
3
ኦሪት ዘፍጥረት 28:16
ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነሥቶ፦ “በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው፥ እኔ አላወቅሁም ነበር” አለ።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:16
4
ኦሪት ዘፍጥረት 28:20-22
ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፥ ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፥ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከዐሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።”
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:20-22
5
ኦሪት ዘፍጥረት 28:14
ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:14
6
ኦሪት ዘፍጥረት 28:19
ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፥ አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:19
គេហ៍
ព្រះគម្ពីរ
គម្រោងអាន
វីដេអូ