1
የዮሐንስ ወንጌል 15:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ብዙ ፍሬ የሚያፈራው በእኔ የሚኖርና እኔም በእርሱ የምኖርበት ነው፤ ነገር ግን ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም።
ប្រៀបធៀប
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:5
2
የዮሐንስ ወንጌል 15:4
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ጸንቶ ካልኖረ በቀር በራሱ ብቻ ፍሬ ማፍራት እንደማይቻለው እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:4
3
የዮሐንስ ወንጌል 15:7
በእኔ ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የፈለጋችሁትን ብትለምኑ ታገኛላችሁ።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:7
4
የዮሐንስ ወንጌል 15:16
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:16
5
የዮሐንስ ወንጌል 15:13
ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:13
6
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:2
7
የዮሐንስ ወንጌል 15:12
የእኔ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:12
8
የዮሐንስ ወንጌል 15:8
ብዙ ፍሬ ስታፈሩ በዚህ አባቴ ይከብራል፤ እናንተም የእኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ታሳያላችሁ።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:8
9
የዮሐንስ ወንጌል 15:1
“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው፤
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:1
10
የዮሐንስ ወንጌል 15:6
በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:6
11
የዮሐንስ ወንጌል 15:11
ይህን የነገርኳችሁ ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና የእናንተም ደስታ ፍጹም እንዲሆን ነው።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:11
12
የዮሐንስ ወንጌል 15:10
እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ፈጸምኩና በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም የእኔን ትእዛዝ ብትፈጽሙ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:10
13
የዮሐንስ ወንጌል 15:17
እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:17
14
የዮሐንስ ወንጌል 15:19
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
រុករក የዮሐንስ ወንጌል 15:19
គេហ៍
ព្រះគម្ពីរ
គម្រោងអាន
វីដេអូ