1
ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።
ប្រៀបធៀប
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
2
ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
ከዚህ በኋላ ሰውየው “ሌሊቱ ሊነጋ ስለ ሆነ ልቀቀኝ” አለ። ያዕቆብም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
3
ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
እርሱ ግን በስተማዶ ለብቻው ቀረ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ አንድ ሰው ሲታገለው ዐደረ።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
4
ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
5
ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
ያ ሰው ያዕቆብን በትግል ማሸነፍ እንዳቃተው ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ መታው፤ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
6
ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
ሰውየውም “ስምህ ማን ነው?” አለው። “ስሜ ያዕቆብ ነው” አለው።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
7
ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
ያዕቆብም “አንተስ ስምህ ማን ነው?” አለው። ሰውየውም “ስሜን ለማወቅ የምትፈልገው ለምንድን ነው?” አለውና ያዕቆብን ባረከው።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
8
ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
9
ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
10
ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ሆይ! ልመናዬን አድምጥ፤ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እዚያም መልካም ነገር እንዲሆንልህ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ ነበር።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
11
ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
គេហ៍
ព្រះគម្ពីរ
គម្រោងអាន
វីដេអូ