1
ኦሪት ዘፍጥረት 28:15
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አይዞህ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበትም ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህም ምድር በደኅና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።”
ប្រៀបធៀប
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:15
2
ኦሪት ዘፍጥረት 28:13
እግዚአብሔርም በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለትውልድህ እንዲሆን ይህን የተኛህበትን ምድር እሰጥሃለሁ፤
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:13
3
ኦሪት ዘፍጥረት 28:16
ያዕቆብም ከእንቅልፉ ነቃና “በእርግጥ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር” አለ።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:16
4
ኦሪት ዘፍጥረት 28:20-22
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ፦ “ከእኔ ጋር ሆነህ በምሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፥ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፥ ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብትመልሰኝ፥ አንተ አምላኬ ትሆናለህ፤ ይህ ለመታሰቢያነት ያቆምኩት ድንጋይ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሁሉ ከዐሥር አንዱን እጅ ለአንተ እሰጣለሁ።”
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:20-22
5
ኦሪት ዘፍጥረት 28:14
ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:14
6
ኦሪት ዘፍጥረት 28:19
ያንንም ስፍራ “ቤትኤል” ብሎ ሰየመው፤ ይህ ስፍራ ከዚያ በፊት ሎዛ እየተባለ ይጠራ ነበር።
រុករក ኦሪት ዘፍጥረት 28:19
គេហ៍
ព្រះគម្ពីរ
គម្រោងអាន
វីដេអូ