YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 14

14
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
# መዝ. 10፥4፤ 36፥2፤ ኢሳ. 32፥6፤ ኤር. 5፥12፤ ሮሜ 3፥10-12። አላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል።
በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉ፥
በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።
2 # ሮሜ 3፥11-12። የሚያስተውል እግዚአብሔርንም? የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ
ጌታ ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።#መዝ. 11፥4፤ 102፥20።
3 # መዝ. 12፥1። ሁሉም ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ፥
በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፥ አንድም እንኳ የለም።
4 # መዝ. 27፥2፤ 79፥6፤ ኢሳ. 9፥11። ክፉ አድራጊዎች አያስተውሉምን?
እንጀራን እንደሚበሉ ሕዝቤን የሚያኝኩ፥
ጌታን አይጠሩምን፥
5እዚያም ታላቅ ፍርሃት ይዞአቸዋል፥
አግዚአብሔር በጻድቃን ዘንድ ነውና፥
6የምስኪኖችን ዕቅድ ታዛባላችሁ፥
ጌታ ግን መጠለያቸው ነው፥
7 # መዝ. 85፥2። ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል?
ጌታ የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥
ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝሙረ ዳዊት 14