YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 13

13
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 6፥4፤ 44፥25፤ 77፥8፤ 79፥5፤ 89፥47፤ 94፥3፤ ሰቆ.ኤ. 5፥20። አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ?
እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?
3እስከ መቼ በነፍሴ እጨነቃለሁ?
ትካዜስ እስከ መቼ ዕለቱን በሙሉ በልቤ ይሆናል?
እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይሸልላል?
4አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፥
ለሞትም እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ
5 # መዝ. 38፥17። ጠላቴ፦ “አሸነፍሁት እንዳይል”፥
የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው።
6 # መዝ. 116፥7። እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥
ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
ለረዳኝን ጌታ እዘምራለሁ፥
መልካምን አድርጎልኛልና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝሙረ ዳዊት 13