YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 96

96
መዝሙር 96
96፥1-13 ተጓ ምብ – 1ዜና 16፥23-33
1እግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤
ምድር ሁሉ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
2እግዚአብሔር ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤
ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ።
3ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፣
ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።
4 እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴውም ብዙ ነው፤
ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል።
5የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤
እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
6ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤
ብርታትና ክብርም በመቅደሱ ውስጥ አሉ።
7የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤
ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።
8ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤
መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤
9በተቀደሰ ውበት ለእግዚአብሔር ስገዱ፤
ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ።
10በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ነገሠ” በሉ፤
ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም፤
እርሱ ለሕዝቦች በእኩልነት ይፈርዳል።
11ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤
ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤
12መስኩና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ፤
ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፤
13እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤
በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤
በዓለም ላይ በጽድቅ፣
በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይፈርዳል።

Currently Selected:

መዝሙር 96: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝሙር 96