መዝሙር 95
95
መዝሙር 95
1ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤
በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።
2ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤
በዝማሬም እናወድሰው።
3 እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤
ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።
4የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤
የተራራ ጫፎችም የርሱ ናቸው።
5እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።
6ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤
በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤
7እርሱ አምላካችን ነውና፤
እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣
የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን።
ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣
8በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣#95፥8 ማሳህ ፈተና ማለት ነው።
በመሪባም#95፥8 መሪባ ጠብ ማለት ነው። እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።
9ሥራዬን ቢያዩም፣
አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።
10ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤
እኔም፣ “በልቡ የሳተ ሕዝብ ነው፤
መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።
11ስለዚህ እንዲህ ብዬ በቍጣዬ ማልሁ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም።”
Currently Selected:
መዝሙር 95: NASV
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.