መዝሙር 149
149
መዝሙር 149
1ሃሌ ሉያ።#149፥1 አንዳንዶች ከ9 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።
ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤
ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ።
2እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤
የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ።
3ስሙን በሽብሸባ ያመስግኑ፤
በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት።
4 እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤
የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።
5ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤
በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።
6የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣
ባለሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤
7በዚህ ሕዝቦችን ይበቀላሉ፤
ሰዎችንም ይቀጣሉ፤
8ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣
መኳንንታቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፤
9ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው።
ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት።
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙር 149: NASV
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.