YouVersion Logo
Search Icon

ዘሌዋውያን 18

18
1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) አምላካችሁ (ኤሎሂም) ነኝ፤ 3በኖራችሁበት በግብፅ እነርሱ እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነዓን እንደሚያደርጉትም አታድርጉ፤ ልማዳቸውንም አትከተሉ። 4ሕጌን ታዘዙ፤ ሥርዐቴንም በጥንቃቄ ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ። 5ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እነዚህን የሚጠብቅ በሕይወት ይኖርባቸዋልና፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።
6“ ‘ማንም ሰው ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ማንኛውም የሥጋ ዘመዱ አይቅረብ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።
7“ ‘ከእናትህ ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም አባትህን አታዋርድ፤ እናትህ ናት፤ ከእርሷ ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።
8“ ‘ከአባትህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አባትህን ያዋርዳል።
9“ ‘ከእኅትህ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፣ ከአባትህ ወይም ከእናትህ ሴት ልጅ ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።
10“ ‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አንተን ያዋርዳል።
11“ ‘የአባትህ ሚስት፣ ለአባትህ ከወለደቻት ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እኅትህ ናት።
12“ ‘ከአባትህ እኅት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እርሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት።
13“ ‘ከእናትህ እኅት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እርሷ የእናትህ የሥጋ ዘመድ ናትና።
14“ ‘ከአባትህ ወንድም ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም፣ የአባትህን ወንድም አታዋርድ፤ እርሷ አክስትህ ናት።
15“ ‘ከምራትህ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከእርሷም ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።
16“ ‘ከወንድምህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ ወንድምህን ያዋርዳል።
17“ ‘ከእናቲቱና ከሴት ልጇ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እነርሱ የሥጋ ዘመዶቿ ናቸው፤ ይህም ጸያፍ ነው።
18“ ‘ሚስትህ በሕይወት እያለች እኅቷን ጣውንት አድርገህ አታግባት፤ ከእርሷም ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም።
19“ ‘በወር አበባዋ ርኩሰት ጊዜ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ሴት አትቅረብ።
20“ ‘ከባልንጀራህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም፣ ራስህን በእርሷ አታርክስ።
21“ ‘ከልጆችህ ማንኛውንም ለሞሎክ እንዲሠዋ#18፥21 ወይም በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አሳልፈህ አትስጥ፤ የአምላክህንም (ኤሎሂም) ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።
22“ ‘ከሴት ጋር እንደሚደረገው ሁሉ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ይህ አስጸያፊ ነው።
23“ ‘ከእንስሳ ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም ራስህን አታርክስ። ሴትም ከእንስሳ ጋር ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ራሷን አታቅርብ፤ ይህ አስጸያፊ ምግባር ነው።
24“ ‘ከእነዚህ በአንዱ እንኳ ራሳችሁን አታርክሱ፤ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ በእነዚህ ሁሉ ረክሰዋልና። 25ምድሪቱም ሳትቀር ረከሰች፤ እኔም ስለ ኀጢአቷ ቀጣኋት፤ ስለዚህ የሚኖሩባትን ሰዎች ተፋቻቸው። 26እናንተ ግን ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እናንተ የአገር ተወላጆችና በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም አትፈጽሙ። 27ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ስለ ፈጸሙ፣ ምድሪቱ ረክሳለች። 28እናንተም ምድሪቱን ብታረክሷት፣ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እንዲሁ እናንተንም ትተፋችኋለች።
29“ ‘ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም የሚፈጽም ሰው ሁሉ ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ። 30ትእዛዜን ጠብቁ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች ካደረጓቸው አስጸያፊ ድርጊቶች አንዱንም አትፈጽሙ፤ በእነዚህም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።’ ”

Currently Selected:

ዘሌዋውያን 18: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy