YouVersion Logo
Search Icon

ዕብራውያን 1

1
የእግዚአብሔር የመጨረሻ ቃል–ልጁ
1እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በተለያየ ጊዜና በልዩ ልዩ መንገድ በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ፣ 2በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን። 3እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ። 4ስለዚህ የወረሰው ስም ከመላእክት ስም እንደሚበልጥ ሁሉ፣ እርሱም ከመላእክት እጅግ የላቀ ሆኗል።
5እግዚአብሔር፣
“አንተ ልጄ ነህ፤
እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤”#1፥5 ወይም እኔ ዛሬ አባት ሆንሁህ መዝ 2፥7
ወይስ ደግሞ፣
“እኔ አባት እሆነዋለሁ፤
እርሱም ልጄ ይሆናል”#1፥5 2ሳሙ 7፥14፤ 1ዜና 17፥13
ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው? 6ደግሞም እግዚአብሔር በኵሩን ወደ ዓለም ሲያስገባ፣
“የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ#1፥6 ዘዳ 32፥43 (የሙት ባሕር ጥቅልሎችንና ሰብዓ ሊቃናትን ይመልከቱ።) ይስገዱለት”
ይላል። 7ስለ መላእክትም ሲናገር፣
“መላእክቱን ነፋሳት፣
አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል”#1፥7 መዝ 104፥4
ይላል። 8ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤
“አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤
የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ይሆናል።
9ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣
የደስታንም ዘይት ቀባህ።”#1፥9 መዝ 45፥6፤ 7
10ደግሞም እንዲህ ይላል፤
“ጌታ ሆይ፤ አንተ
በመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤
ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።
11እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤
ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤
12እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤
እንደ ልብስም ይለወጣሉ።
አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤
ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”#1፥12 መዝ 102፥25-27
13እግዚአብሔር፣
“ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ እስከማደርግልህ ድረስ፣
በቀኜ ተቀመጥ”#1፥13 መዝ 110፥1
ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው? 14መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?

Currently Selected:

ዕብራውያን 1: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in