1
መጽሐፈ መክብብ 9:10
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ባለህ ኀይል ሥራህን ሁሉ በትጋት ፈጽም፤ ወደ ሙታን ዓለም ከወረድህ በኋላ በዚያ ሥራና ሐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ የለም።
Compare
Explore መጽሐፈ መክብብ 9:10
2
መጽሐፈ መክብብ 9:11
በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤
Explore መጽሐፈ መክብብ 9:11
3
መጽሐፈ መክብብ 9:9
በዚህ ዓለም እግዚአብሔር በሰጠህ ከንቱ በሆነ ኑሮህ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ ስለ መከራህና ስለ ድካምህ ሁሉ ዋጋ ሆኖ የተሰጠህ ዕድል ፈንታ ይኸው ብቻ ስለ ሆነ ከንቱ ዘመንህን፥ እያንዳንዱን ቀን ተደሰትበት።
Explore መጽሐፈ መክብብ 9:9
4
መጽሐፈ መክብብ 9:7
እግዚአብሔር ቀድሞ የፈቀደልህ ይህ በመሆኑ ሂድ፤ ምግብህን ተመግበህ፥ የወይን ጠጅህንም ጠጥተህ በመርካትህ ደስ ይበልህ።
Explore መጽሐፈ መክብብ 9:7
5
መጽሐፈ መክብብ 9:18
ከጦር መሣሪያ ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ ነገር ግን አንድ ኃጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።
Explore መጽሐፈ መክብብ 9:18
6
መጽሐፈ መክብብ 9:17
በሞኞች ጉባኤ ከሚሰማው የአገረ ገዥ የጩኸት ድምፅ ይልቅ በዝግታ የሚነገር የጥበበኛ ቃል ይሻላል።
Explore መጽሐፈ መክብብ 9:17
7
መጽሐፈ መክብብ 9:5
በሕይወት ያሉ ሰዎች አንድ ቀን እንደሚሞቱ ያውቃሉ፤ ሙታን ግን አንዳች ነገር አያውቁም፤ ፈጽሞ የተረሱ በመሆናቸውም ዋጋ የላቸውም።
Explore መጽሐፈ መክብብ 9:5
Home
Bible
Plans
Videos